የቬልትሁንገርሂልፈ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ የምግብ እና የስርአተ ምግብ ዋስትና ለማሻሻል ይሰራል፤ በዚህ አካባቢ የምግብ ዋስትና በድርቅ እና በአሰቸጋሪ የአየር ንብረትና በሰው ሰራሽ በስጋት ላይ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ የቬልትሁንገርሂልፈ በቤተሰብ ደረጃ የተቀናጁ ፕሮግራሞች ቀጣይነት ያለው የምግብ እና የስርአተ ምግብ ዋስትና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን፣ ለዚህ ልዩ ልዩ ዘርፎች ለምሳሌ ግብርናን፣ አካባቢን፣ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ልማትን፣ ውሃን፣ ንፅህናና፤ ጤናን፤ የሥነ ምግብ ትምህርትን እና የማኅበረሰብ አባላት ስለ ዓለም ዓቀፍ ኔትወርክ እና ስለ ሥነ ጾታ ንቁ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአደጋ ስጋት ቅነሳን፣ ሰብዓዊ እርዳታን፣ ችግረን የመቐቐም ግንባታን እና ልማትን እናያይዛለን፡፡
ከአጋሮቻችን ጋር በጋራ በመሆን፣ በማኀበረሰቦች በራሳቸው በተለዩ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ተመስርተን እንሰራለን፡፡ የአካባቢውን ጥበብ እና እውቀት ከወቅቱ የቴክኒክ እውቀት ጋር ከዓለም ዓቀፍ ዕውቀት ጋር አናጣምራለን፡፡ ይህም አብረናቸው ለምንሰራባቸው ማኅበረሰቦች ትርጉም ያላቸው ብሔራዊ እና ዓለም ዓቀፍ ፖሊሲዎች እና ስታንዳርዶች አስተዋጽዖ እንድናደርግ ያግዘናል፡፡
በሶማሌላንድ፣ የቬልትሁንገርሂልፈ የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ በመስጠት ሰዎች ያጋጠሟቸውን አጣዳፊ ችግሮች ይፈታል፤ ነገር ግን ለድህነት እና ለረሃብ ምክንያት መነሾ የሆኑትን ዋነኛ ምክንያቶች በመለየት የረጅም ጊዜ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ ከእነርሱም መካከል የተፈጥሮ ኃብቶች አመራር፣ መሠረታዊ ትምህርት፣ በገበያ ማቀናጀት ገቢ ማስገኘት፣ ግብርና እና ከሁኔታዎች ጋር መጣጣምን ማሻሻል እንዲሁም የአደጋ ዝግጁነት ማኅበረሰቦች ይገኙባቸዋል፡፡
ፕሮጀክቶቻችን በዋናነት የአነሰተኛ እርሻ ባለይዞታ አርሷደሮችን፣ በግብርናና በከብት እርባታ የተሰማሩ አርቢዎችን፣ ተፈናቃዮችን፣ ሴቶችን እና ልጆችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትና የትኩረት ጉዳዮች
“በምንሰራባቸው አካባቢዎች ዜሮ ረሃብን ማረጋገጥ” በሚል በተቀመጠው ዓለም ዓቀፍ ግብ መሠረት፣ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በማኅበረሰብ ደረጃ ቀጣይነት ያለው የምግብ እና የሥነ ምግብ ደህንነት ከማረጋገጥ አንጻር የራሳችንን አስዋጽዖ እናደርጋለን፡፡ ይህንንም “ኦል ፎር ሰም አፕሮች” ብለን እንጠራዋለን፡፡
እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ለድርጅታችን ውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንጽሕና ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በከተማ እና ንዑስ ገጠር አካባቢዎች የአነስተኛ የእርሻ መሬት ባለይዞታ አርሷደሮችን እና አግሮ-ፓስቶራሊስቶች ፍላጎቶችን ያሟላል፡፡ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ ዋነኛ የምግብ እጥረት ምክንያት እንደመሆኑ መጠን፣ የሥነ ምግብ ዕውቀትን ከንፁህ መጠጥ ውሃ፤ የአካባቢ ፅዳትና ስነ ንፅህና ፕሮግራሞች ጋር አጣምረን ቀጣይ ትኩረት በመስጠት እየሰራን እንገኛለን፡፡ ቀጣይነት ላላቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ሲስተሞች እና በክልሉ በየንፁህ መጠጥ ውሃ፤ የአካባቢ ፅዳትና ስነ ንፅህና መሠረተ ልማቶች የሚገኘውን የኢንቬስትመንት ትርፍ ከፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡
በተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች፣ በመስኖ፣ ከገቢ ማስገኛ ሥራዎች ጋር በተያያዘ በተፈጥሮ ኃብቶች አያያዝ፣ ገበያን በማቀናጀት፣ በግብርና ሥራዎች የማቀነባበር እና የግብይት ሥራ እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ የባለ አነስተኛ እርሻ መሬት አርሷደሮችን የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትና የማጠናከር ዕቅድ አለን፡፡ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ ድርቅን መቋቋም እና ለአፈር ለምነት የአካባቢን ኃብቶች በተሻለ መጠቀም በግብርና ዘርፍ አዳዲስ ፈጠራ ለማምጣት ወሳኝ ናቸው፡፡
ለሰሴቶች እና መሬት ለሌላቸው ወጣቶች በዚህ ሰነድ በተገለጹ ሌሎች የልማት አቅጣጫዎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንሰራለን፡፡ በተጨማሪ በሲቪል ማኅበረሰቦች እና በመንግሥት አካላት መካከል በተለያዩ ደረጃዎች በሚደረጉ ውይይቶች እነዚህ ተጠቃሚ ያልሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲኖራቸው እናደርጋለን፡፡
የቬልትሁንገርሂልፈ ድጋፍ በፌያደረግባቸው አካባቢዎች የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ በመስጠጥ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ከዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ እና ከኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መንግሥታት ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ ይህንንም ለማገዝ፣ እርዳታን፣ መልሶ ማቋቋምን እና ቀጣይነት ያለውን ልማት በማጣመር ለዋነኛ የአደጋ ምክንቶች መፍትሔ እንሰጣለን፡፡
Selected projects in Horn of Africa