ማንነታችን
የቬልትሁንገርሂልፈ በጀርመን ትልቁ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ከማናቸውም የፖሊቲካም ሆነ የኃይማኖት ትስስር ነጻ ነው፡፡ ይህ ድርጀት የተመሠረተው በ1962 በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ጥላ ስር ነው፡፡ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ፣ ከ9331 ከ70 በላይ በሆኑ የተለያዩ አገራት ፕሮጀክቶች መስርቷል፡፡ እነዚህም ድርጅቶች የ3.71 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አግኝተዋል፡፡ የቬልትሁንገርሂልፈ ዋነኛው መርህ ራስን ለመርዳት መርዳት የሚል ነው፡- ከአካባቢ ወይም የአገር ውስጥ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን መዋቅሮችን ከታች ወደላይ እናጠናክራለን፤ ለፕሮጀክት ሥራችንም የረጅም ጊዜ ስኬት ጥረት እናደርጋለን፡፡