ወደ ዋናው ገፅ ለመሄድ

ቬልትሁንገርሂልፈ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ

© Welthungerhilfe Ethiopia
© Welthungerhilfe Ethiopia

ቬልትሁንገርሂልፈ (ጀርመን አግሮ አክሽን በሚል ስያሜ የተመዘገበ) ከ1972 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በሶማሌላንድ ደግሞ የተመሰረተው በ2001 ነበር፡፡ ዋነኛው ግባችን ቀጣይነት ያለው የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው፡፡ እስከዛሬው ቀን ድረስ፣ 252 ፕሮጀክቶች በመንግሥታት፣ በብሔራዊ እና ዓለም ዓቀፍ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ዒላማ በተደረጉ ማኅበረሰቦች ትብብር አማካኝት ተተግብረዋል፡፡ የቬልትሁንገርሂልፈ ክልላዊ መሥሪያ ቤት የሚገኘው በአዲስ አበባ ሲሆን፣ 41 ሠራተኞች አሉት፡፡ የአገሪቱ መዋቅር አምስት የመስክ መሥሪያ ቤቶች በጅማ፣ ቱሉቦሎ፣ ደብረ ማርቆስ እና አፋር አሉት፡፡ የሶማሌላንድ የፕሮግራም መሥሪያ ቤት የሚገኘው በሀርጌሳ ሲሆን፣ የመስክ መሥሪያ ቤቱ ደግሞ በቦሮማ ይገኛል፤ በአሁኑ ወቅት 53 ሠራተኞች አሉት፡፡

ርሃብን ከ አፍሪካ ቀንድ ማጥፋት 

በቬልትሁንገርሂልፈ በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት ይዘት ተኮር እርሻ ቴክኒኮች እና የተፈጥሮ ኃብቶች አስተዳደር እንዲኖር ጥረት ያደርጋል፤ ለምናገለግላቸው ማኅበረሶች የሚቀርበውን ምግብ ዓይነት እና መጠን ለማሳደግ ምርትንና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ከዚህም ሌላ ለሴቶች እና እናቶች በሥነ ምግብ ዝግጅት ላይ እውቀትን ስለማካፈል ትኩረት እንሰጣለን፡፡ የምንከተለው ጠቅለል ያለ አካሄድ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ደህንነቱ የተጠበቀ ውሃ ተደራሽነት፣ የአካባቢ እና የግል ንጽሕና መጠበቅ ናቸው፡፡ 

Emergency aid during drought in Borana, Ethiopia

ስለ ፕሮጀክቶቻችን እና ስለ ፕሮግራማችን ለማወቅ

ሌላው ዓላማ ደግሞ አብረናቸው ለምንሰራቸው ሰዎች የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎችን ዓይነት ማብዛት ነው፡፡ ስለዚህ ቬልትሁንገርሂልፈ በአፍሪካ ቀንድ ተወዳዳሪ እና ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በማኅበራዊ ሥራ እና የኢኮኖሚ እድገት ፕሮግራም አማካኝነት በውድድር ላይ የተመሠረተ ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በመስራት ላይ ነው፡፡

እነዚህ የልማት እንቅስቃሴዎች ሁኔታዎችን ለማቋቋም እና ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች እና ለማኅበረሰቡ ምላሽ ለመስጠት በሰብዓዊ ድጋፍ የተቃኙ ናቸው፡፡

ከእነዚህ የረጅም ጊዜ የሥራ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ፣ ቬልትሁንገርሂልፈ ምሥራቅ አፍሪካ በተለያዩ ችግሮች ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ይሰጣል እንዲሁም የተጎዱ የማኅበረሰብ አባላትን የመቋቋም ችሎታ ያጠናክራል፡፡