ወደ ዋናው ገፅ ለመሄድ
Crops grown from irrigation system near Ruqi village in Somaliland

ረሀብን ማጥፋት

በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚከናወነው የግብርና ሥራ ለእያንዳንዱ ሰው  በቂ ምግብ ያመርታል፡፡ ነገር ግን ክፍፍሉ እጅግ በከፋ መልኩ ያልተመጣጠነ ነው፡፡  በተባበሩት መንግስታት ዘላቂ ልማት ግብ እስከ 2030 (እኤአ) ረሀብን ማጥፋት በሚለው ላይ ተመስርተን ስለምንሰራ ቬልትሁንገር ሂልፌ በሚያከናውናቸው ሥራዎች ሁሉ  ይህን ለምግብ ያለውን ሰብዓዊ መብት ማዕከሉ ያደርጋል፡፡

የረሀብ  መንስኤዎች

ረሀብ ከሁሉ በላይ የድህነት ውጤት ነው፡፡ ለምግብ ወጪ በቂ ገንዘብ የሌላቸው ቤተሰቦች ጤናቸውን ለመጠበቅም ሆነ የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪ ለመሸፈን አይችሉም፡፡

ረሀብ አብዛኛውን ጊዜ ከመሀል አገር ርቀው በሚገኙ የዓለም አካባቢዎችን ያጠቃል፡፡ በሩቅ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ምግባቸውና የኑሮ መሰረታቸው በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡በገጠር ማህበረሰቦች ዘንድ የምግብ ዋስትናው በትጥቅ በታገዘ ግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና እንደ የተራዘመ ዝናብ ወይም ድርቅ ባሉ የአየር ለውጥ ጫና ምክንያት የተወሳሰበ ነው፡፡

በከፍተኛ የረሀብ ደረጃ የሚጠቁ አገሮች ብዙውን ጊዜ ሚዛናዊ ያልሆነ የንግድ ሁኔታዎች የሚገጥማቸው ናቸው፡፡  በዓለምአቀፍ ገበያ ላይ የሚቀርበው የምግብና የግብርና ጥሬ ዕቃዎች ከፍተኛ  ፍጆታ ብዙዎቹ ጤናማ ምግብ ለመግዛት አቅሙ የሌላቸውን የገጠር ቤተሰቦችን የምግብና የተመጣጠነ/አልሚ ምግብ ዋስትናን ይፈታተናል፡፡

በነዚህ አገሮች የሰፈነው መበላለጥ የመጨረሻ ደሀ የሆኑትን ዜጎች ማህበራዊና የተሰሚነት ደረጃ ያዳክማል፡፡ ይህም ድህነትን ያባብሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ብልሹ አስተዳደርና እንደ መሬት ወረራ ያሉ የሙስና ዓይነቶች ልማትን ወደማደናቀፍ ያመራሉ፡፡

 ረሀብ የሚያስከትላቸው ውጤቶች

ዛሬ በዓለምአቀፍ ደረጃ ከስምንት መቶ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ በረሀብ አደጋ በመጠቃት ላይ ይገኛል፡፡በሁለት ቢሊዮን የሚገመት ሕዝብ ደግሞ ጠቃሚ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን አያገኝም፡፡ ይህ ሁኔታ የተደበቀ ረሀብ (የምግብ እጥረት) (hidden hunger) መከሰቻ ተብሎ ይታወቃል፡፡ረሀብና የአልሚ ምግብ እጥረት የአካባቢዎችን አጠቃላይ ልማት ያደናቅፋል፡፡ ይህም በማህበረሰብ ብቃትና ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ የበለጠ ተጋላጮች ደግሞ በተለምዶ የሚታወቁትና ከፍተኛ ሰለባ የሆኑት ሕጻናት ናቸው፡፡

በባህላዊ ማህበረሰቦች መዋቅር ላይ የተመሰረተ መበላለጥ የተነሳ ሴቶች ለመማር ያላቸው ተደራሽነት ወይም ለሕይወት መሰረት ያላቸው ዕድል ዝቅተኛ ነው፡፡ አብዛኞቹ የራሳቸው የሆነ ሀብት የላቸውም፡፡ ብዙውን ጊዜ ደግሞ በእርሻ ሥራዎችና ሕጻናትን የማሳደግ ኃላፊነት የተጠመዱ ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በአልሚ ምግብና በግል ንጽሕና አጠባበቅ ላይ እውቀቱ ስለሌላቸው በሕጻናት ጤና ላይ አደጋው ይጨምራል፡፡

በቂና የተመጣጠነ ምግብ ለነፍሰጡር እናቶች፣ ለሚያጠቡ እናቶችና በመጀመሪያው አንድ ሺህ (1000) ቀናት የሕይወት ዘመናቸው ላይ ለሚገኙ ሕጻናት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሕጻናትን የተፈጥሮ የመከላከያ አቅም ያዳክማል፡፡ በተጨማሪም ከአጠቃላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር ተዳምሮ በቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ለአካል ጉድለትና ለአነስተኛ የአእምሮ እድገት ይዳርጋቸዋል፡፡

መንስዔዎቹን መዋጋት

የቬልትሁንገርሂልፈ እስትራቴጃዊ ትኩረት ከሁሉ በላይ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ዘላቂ የምግብና የተመጣጠነ ምግብ (አልሚ ምግብ) ዋስትናን ማስገኘት ነው፡፡  ከማህበረሰቡና ከተባባሪድርጅቶች ጋር በቅርበት በመተባበር ፕሮጄክቶቻችን የምግብና የኢኮኖሚ ሥርዓት ክፍተቶች መፍትሔ ለማስገኘት ይሰራሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉትም የከፋ፣ለረጅም ጊዜ የቆየና ድብቅ ረሀብን ለማጥፋት ነው፡፡ ይህን ግብ ለማሳካት የምንከተላቸው የአሰራር ዘዴዎች አሉን፡፡ እነዚህም በተወሰነ አካባቢ ላይ የሚከናወን እርሻ፣ ለአካባቢው ሁኔታና ለሕዝብ ባህል የሚስማማ የአመራረት ዘዴና የእህል ዓይነት፣ የሕዝቡን የመቋቋም አቅም ማጠናከር፣ የተቃወሱ ሁኔታዎችና አደጋዎች  በሚከሰቱበት ጊዜ ማህበረሰቦችን ማዘጋጀትና  ቀውሶቹና አደጋዎቹ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖመቀነስና ሲቭል ማህበረሰቦችን ማጠናከር፣ የተገለሉ ሕዝቦች መብታቸውን እንዲጠይቁ ድምጻቸውን ከፍ አድርጎ ማሰማት አንዳንዶቹ ናቸው፡፡

Adult education class in Boon, Somaliland © Welthungerhilfe

ዓለምአቀፍ ረሀብን የመታገል የአሠራር ዘዴዎቻችንን የበለጠ ይገንዘቡ፡፡

 የረሀብ ፍጻሜ መቃረብ 

በረሀብ መንስኤዎች ላይ የምንሰራ በመሆናችን በዓለምአቀፍ ደረጃ ረሀብን ለማጥፋት ጉልህ ጥረቶች እየተከናወኑ ናቸው፡፡ የዛሬ ሁለት መቶ ዓመት ከአስር ሰዎች ወደ ዘጠኝ የሚጠጉት የመጨረሻ ደሀ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ ከአስር ሰዎች አንዱ ነው፡፡ የቬልትሁንገርሂልፈ ዓመታዊ የድህነት መግለጫ እንደሚያመለክተው ባለፉት 15 ዓመታት ጥናት በተካሄደባቸው ሁሉም አገሮች ድህነት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ በአፍሪካ በአማካይ የሰላሳ በመቶ  ቅነሳ ነበር፡፡  በመጨረሻም ቬልት ሁንገር ሂልፈ ከተቋቋመበት ካለፉት 50 ዓመታት ጀምሮ የሕጻናት ሞት ከደቡባዊው የዓለም ክፍል ከሃያ በመቶ ወደ አምስት በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡