ወደ ዋናው ገፅ ለመሄድ
Emergency aid during drought in Borana, Ethiopia

እኛ ምን እንሰራለን

የቬልትሁንገርሂልፈ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ የምግብ እና የስርአተ ምግብ  ዋስትና ለማሻሻል ይሰራል፤ በዚህ አካባቢ የምግብ ዋስትና በድርቅ እና በአሰቸጋሪ የአየር ንብረትና በሰው ሰራሽ  በስጋት ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የቬልትሁንገርሂልፈ በቤተሰብ ደረጃ የተቀናጁ ፕሮግራሞች ቀጣይነት ያለው የምግብ እና የስርአተ ምግብ ዋስትና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን፣ ለዚህ ልዩ ልዩ ዘርፎች ለምሳሌ ግብርናን፣ አካባቢን፣ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ልማትን፣ ውሃን፣ ንፅህናና፤ ጤናን፤  የሥነ ምግብ ትምህርትን እና የማኅበረሰብ አባላት ስለ ዓለም ዓቀፍ ኔትወርክ እና ስለ ሥነ ጾታ ንቁ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአደጋ ስጋት ቅነሳን፣ ሰብዓዊ እርዳታን፣ ችግረን የመቐቐም ግንባታን እና ልማትን እናያይዛለን፡፡

ከአጋሮቻችን ጋር በጋራ በመሆን፣ በማኀበረሰቦች በራሳቸው በተለዩ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ተመስርተን እንሰራለን፡፡ የአካባቢውን ጥበብ እና እውቀት ከወቅቱ የቴክኒክ እውቀት ጋር ከዓለም ዓቀፍ ዕውቀት ጋር አናጣምራለን፡፡ ይህም አብረናቸው ለምንሰራባቸው ማኅበረሰቦች ትርጉም ያላቸው ብሔራዊ እና ዓለም ዓቀፍ ፖሊሲዎች እና ስታንዳርዶች አስተዋጽዖ እንድናደርግ ያግዘናል፡፡

በሶማሌላንድ፣ የቬልትሁንገርሂልፈ የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ በመስጠት ሰዎች ያጋጠሟቸውን አጣዳፊ ችግሮች ይፈታል፤ ነገር ግን ለድህነት እና ለረሃብ ምክንያት መነሾ የሆኑትን ዋነኛ ምክንያቶች በመለየት የረጅም ጊዜ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ ከእነርሱም መካከል የተፈጥሮ ኃብቶች አመራር፣ መሠረታዊ ትምህርት፣ በገበያ ማቀናጀት ገቢ ማስገኘት፣ ግብርና እና ከሁኔታዎች ጋር መጣጣምን ማሻሻል እንዲሁም የአደጋ ዝግጁነት ማኅበረሰቦች ይገኙባቸዋል፡፡

ፕሮጀክቶቻችን በዋናነት የአነሰተኛ እርሻ ባለይዞታ አርሷደሮችን፣ በግብርናና በከብት እርባታ የተሰማሩ አርቢዎችን፣ ተፈናቃዮችን፣ ሴቶችን እና ልጆችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትና የትኩረት ጉዳዮች

“በምንሰራባቸው አካባቢዎች ዜሮ ረሃብን ማረጋገጥ” በሚል በተቀመጠው ዓለም ዓቀፍ ግብ መሠረት፣ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በማኅበረሰብ ደረጃ ቀጣይነት ያለው የምግብ እና የሥነ ምግብ ደህንነት ከማረጋገጥ አንጻር የራሳችንን አስዋጽዖ እናደርጋለን፡፡ ይህንንም “ኦል ፎር ሰም አፕሮች” ብለን እንጠራዋለን፡፡